ይህ በእ.አ.አ ታኅሳስ 6፣ 2014 ከአየር ላይ የተነሳው ፎቶ የሃማስ ማዘጋጃ ቤት ሕንጻን የሸፈነው የባሻር አል አሳድ ፎቶ ተቃዋሚዎች ከተማዋን መቆጣጠራቸውን ተከትሎ በጥይት ተበሳስቶ ያሳያል።/ኤኤፍፒ/ (AFP)
የሶሪያ የለውጥ ሂደት
የአሳድ ውድቀት የመጣው ከዓመታት ደም መፋሰስ እና ክፍፍል በኋላ ነው
የሶሪያ መሪ ባሻር አል አሳድ አገዛዝ ድንገተኛ አወዳደቅ፣ 14 ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ የተካሄደ አመፅ እና፣ በመቶ እና ሺሕዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተገደሉበት፣ ከሀገሪቱ ሕዝብ ግማሽ የሚኾነው የተፈናቀሉበት እና የውጭ ኃያል ሀገራት የተሳቡበት ቁልፍ ጊዜ ድምር ውጤት ነው። ሂደቱን በቅደም ተከተል እንመልከት
2004 ዓ.ም.
በአሳድ ላይ የተነሳው የመጀመሪያው ተቃውሞ በፍጥነት በመላ ሀገሪቱ ተሰራጨ። የጸጥታ ኃይሎችም በጅምላ እስር እና በተኩስ ምላሽ ሰጡ።
አንዳንድ ተቃዋሚዎች ጠመንጃ አነሱ፣ሕዝባዊ ተቃውሞው ወደ ትጥቅ አመጽ ተቀይሮ ከምዕራብ ሀገራት፣ ከአረብ ሀገራት እና ከቱርክ ድጋፍ ወደሚያገኝበት ሁኔታ ሲሸጋገር ክፍለ ጦሮች መክዳት ጀመሩ።
እ.አ.አ. በ2011 ዓ/ም ታኅሣሥ ወር ግጭት በርክቶባት በነበረችው የማዕከላዊ ሶሪያ ሆምስ ከተማ በተካሄደ ትልቅ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ከተነሳ ቪዲዮ የተወሰደ ምስል ነው፡፡ ተቃውሞ ለማፈን በተወሰደው ርምጃ በርካታ ሰዎች በተገደሉ ማግሥት የዓረብ ሃገራት ታዛቢዎች ጉብኝት ላይ ሳሉ ጎዳና ላይ የወጡትን ወደ 70 ሺሕ የሚጠጉ ሰዎች የሶሪያ ፖሊሶች በአስለቃሽ ጋዝ በትነዋል፡፡ (AFP)
2005 ዓ.ም.
የአል-ቃይዳ አዲስ የሶሪያ አጋር የሆነው “የኑስራው ግንባር” የተባለው ቡድን የመጀመሪያውን የቦምብ ጥቃት ደማስቆ ላይ አደረሰ። ይህንኑ ተከትሎ ቡድኑ ጉልበት እያገኘ ሲሄድ የብሔርተኝነት ርዕዮተ ዓለም የሚያራምዱ ቡድኖችን ማጥቃት ጀመረ።
“ሶሪያዊያን እ.አ.አ ግንቦት 10 ቀን 2012 ዓ/ም ደማስቆ ውስጥ በደረሱ ሁለት ፍንዳታዎች የተገደሉ ሰዎችን አስከሬኖችን ሲያነሱ ይታያሉ ፡፡ በዋና ከተማዋ ደማስቆ ሰዎች ጠዋት ወደ ሥራ በሚጣደፉበት ሰዓት ላይ በተከታታይ በደረሱ ሁለት ከባድ ፍንዳታዎች በርካታ ሰዎች ተገድለዋል፡፡ ብዙዎችም መቁሰላቸውን የዘገበው የመንግሥቱ ቴሌቭዢን ”አሸባሪዎች ያደረሱት ጥቃት“ ሲል ወንጅሏል፡.” (ፎኤኤፍፒ/ኤች ኦ/ ሰንአቶ)
በወቅቱ የዓለም ኃያላን መንግሥታት በጄኔቫ ተገናኝተው የፖለቲካ ሽግግር እንደሚያስፈልግ ቢስማሙም፣ በምን መልኩ ተግባራዊ መሆን እንዳለበት ሊስማሙ ባለመቻላቸው በቀጣዮቹ ዓመታት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ድጋፍ የተካሄዱ የሰላም ጥረቶችን ሲያከሽፍ ቆየ።
አማፂያኑ በምድር ጦር በተካሄዱ ጦርነቶች ድል ማግኘት በመጀመራቸው አሳድ የአየር ኃይላቸውን በተቃዋሚ በተያዙ አካባቢዎች ላይ አዘመቱ። ጦርነቱ በሁለቱም ወገኖች ላይ የሚያደርሰው እልቂትም እያየለ ሄደ።
2004 ዓ.ም.
ሊባኖስ የሚገኘው ሂዝቦላህ፣ የታጣቂዎቹን ኃይል በማዳከም አሳድ ኩሳይር ከተማ ላይ ድል እንዲቀዳጁ ረዳ። በዚህም የአማጽያኑ ግሥጋሴ ተገታ፡፡ በኢራን የሚደገፈው ይህ ቡድን ያለው ሚና እየጎለበተ መሄዱን አሳየ።
እ.አ.አ ነሐሴ 29፣ 2013 ዓ/ም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኬሚካል የጦር መሣሪያዎች አዋቂ ባለሞያ ፊታቸውን በጋዝ መከላከያ ጭንብል ሸፍነው የኬሚካል የጦር መሣሪያ ጥቃት ተፈጸሞበታል የተባለውንና ከደማስቆ ወጣ ብሎ የሚገኘውን ዛማልካ የተባለ ሥፍራ ሲጎበኙ። (ሮይተርስ)
ዋሽንግተን በወቅቱ የኬሚካል ጦር መሣሪያዎች ጥቅም ላይ ማዋል “ቀይ መስመር” መጣስ ነው ስትል ዐውጃ የነበረ ሲሆን፣ በደማስቆ አቅራቢያ በአማፅያኑ ቁጥጥር ስር ትገኝ በነበረችው ምስራቅ ጉታ ላይ በደረሰ የጋዝ ጥቃት በርካታ ሲቪሎች ተገደሉ፡፡ ሆኖም ዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ምላሽ አልሰጠችም።
2005 ዓ.ም
እ.አ.አ ሰኔ 30፣ 2014 ዓ/ም እስላማዊ አስተዳደር ወይም “ካሊፌት” መታወጁን ለማክበር በሰሜናዊ ራካ ክፍለ ግዛት ጎዳናዎች ላይ በተደረገው ወታደራዊ ሰልፍ ላይ እስላማዊ ነውጠኛ ተዋጊዎች ሲሳተፉ።” (ሮይተርስ)
እ.አ.አ ነሐሴ 29፣ 2013 ዓ/ም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኬሚካል የጦር መሣሪያዎች አዋቂ ባለሞያ ፊታቸውን በጋዝ መከላከያ ጭንብል ሸፍነው የኬሚካል የጦር መሣሪያ ጥቃት ተፈጸሞበታል የተባለውንና ከደማስቆ ወጣ ብሎ የሚገኘውን ዛማልካ የተባለ ሥፍራ ሲጎበኙ። እስላማዊ መንግሥት በድንገት በሰሜን ምሥራቅ የሚገኘውን ራቃንና በሶሪያ እና ኢራቅ ግዛት ውስጥ ሰፋት ያላቸው ቦታዎችን ያዘ።
በጥንታዊቷ ሖምዝ ከተማ የሚገኙ አማፂያንም እጃቸውን በመስጠት ከከተማው ለመውጣት መስማማታቸው በትልቅ ከተማ ውስጥ የነበራቸውን የበላይነት ያጡበት የመጀመሪያ ሽንፈታቸው ሆነ። ወደፊት “ይዞታዎቻቸውን ለቆ የመውጣት” ስምምነቶች እንደሚቀጥሉ አመላካች ነበር።
ዋሽንግተን በበኩሏ ፀረ-እስላማዊ መንግሥት ጥምረት በመገንባት የአየር ድብደባ ማካሄድ ጀመረች። ይህ ሁኔታ የኩርድ ኃይሎች የበላይነት እንዲያገኙ ቢረዳም የአሜሪካ አጋር ከሆነችው ቱርክ ጋር ግን ግጭት ፈጠረ።
2008 ዓ.ም
አማፂያኑ ከውጪ የሚያገኙት ትብብር እና የተሻለ የጦር መሣሪያ በምድር ውጊያ የበላይነት ለማግኘት ስለረዳቸው በሰሜን ምዕራብ የምትገኘውን ኢድሊብ ከተማ ለመቆጣጠር ቢችሉም፣ በትግሉ ውስጥ ትልቅ ሚና የነበራቸው እስላማዊ ታጣቂዎች ነበሩ። ሆኖም ሩሲያ የአሳድን ወገን በመደገፍ ጦርነቱን በመቀላቀሏ በቀጣዮቹ ዓመታት አማፂያኑ የነበራቸውን የበላይነት አጡ።
እ.አ.አ መስከረም 30፣ 2015 ዓ/ም የተነሳው ይህ ፎቶ በማዕከላዊ ሶሪያ ሆምስ ክፍለ ግዛት ታልቢሴህ ከተማ ጭር ያሉ ጎዳናዎችን እና የወደሙ ህንጻዎችን የሚያሳይ ነው፡፡ ሩሲያ ሆምስ ከተማ አቅራቢያ በሶሪያ የመጀመሪያዋ የሆነውን የአየር ጥቃት መፈጸሟን መስከረም 30 ቀን አረጋግጣለች፡፡ ጥቃቱም ሞስኮ 4 ዓመት ተኩል ባስቆጠረው ጦርነት ውስጥ በይፋ ጣልቃ መግባት መጀመሯን አመልክቷል፡፡ (ኤኤፍፒ)
የሶሪያ ሲቪል መከላከያ ወይም ባለነጭ ቆብ የተባለው በጎ ፈቃደኛ የጥቃት ሰለባዎችን ፈልጎ አዳኝ ቡድን መስከረም 30፣ 2015 ዓ/ም ትዊተር ገጹ ላይ ያወጣው ምስል በሶሪያ ታልቢሴህ ከተማ በአየር ጥቃት የወደመን አካባቢ ያሳያል፡፡ የሩስያ ፕሬዝደንት ቭላዲሚር ፑቲን እስላማዊ ነውጠኞቹ ጥቃት እንዳያደርሱ ለመከላከል ያለመ ድብደባ እንዳካሄዱ አስታውቀዋል፡፡ (ኤፒ)
2009 ዓ.ም
የኩርድ ኃይሎች ድንበር ላይ የነበራቸው ግሥጋሤ ያሰጋት ቱርክ በበኩሏ ከአማፂያኑ ጋራ በመኾን ወረራ ጀመረች። ይህም በቱርክ ቁጥጥር ሥር የሚገኝ አዲስ ቀጣና ፈጠረ።
እ.አ.አ መስከረም 3፣ 2016 ዓ/ም ከሶሪያ ጋር በሚያዋስነው የቱርክ ካርካሚስ አቅራቢያ የቆሙ የቱርክ ታንኮች ናቸው፡፡ የቱርክ ታንኮች “የኤፍራጥስ መከላከያ ዘመቻ አዲስ ምዕራፍ” ተብሎ የተሰየመውን ዘመቻ ለማካሄድ የሰሜን ምስራቅ አሌፖ ኮባንቢ ወረዳ መግባታቸውን የቱርክ መንግሥት የዜና አገልግሎት አስታውቋል፡፡”(ኤፒ)
አሌፖ ውስጥ የነበሩ አማፂያን በሶሪያ ጦር እና አጋሮቹ መሸነፋቸው አሳድ በጦርነቱ ውስጥ ያገኙት ‘ትልቅ ድል’ ተደርጎ ተቆጥሮ ነበር።
የኑስራ ግንባርም ከአል-ቃኢዳ ተገንጥሎ ራሱን ለዘብ ባለ ቁመና በማቅረብ የተለያዩ ስያሜዎችን ሲጠቀም ከቆየ በኋላ በመጨረሻ ሀያት ጣሂር አል-ሻም በሚል ስያሜ መጠራት ጀመረ።
2010 ዓ.ም.
እስራኤል፣ እየተጠናከረ የሄደውን የኢራን እና የአጋሮቿን ኃይል ለማዳከም፣ ሶሪያ በሚገኘው ሂዝቦላህ ላይ የአየር ድብደባ ማካሄዷን አመነች።
እ.አ.አ ነሐሴ 15፣ 2017 ዓ/ም ራካ ውስጥ በሶሪያ ዲሞክራሲያዊ ኅይሎች አባላት እና በእስላማዊ መንግሥት ታጣቂዎች መካከል በተካሄደ ውጊያ በደረሰ የአየር ጥቃት ከተመታ ሥፍራ ጢስ ሲወጣ ያመለክታል። (ሮይተርስ)
በዩናይትድ ስቴትስ የሚደገፈው በኩርዶች የሚመራው ጦርም ራቃ ላይ እስላማዊ መንግሥትን አሸነፈ። ይህ ጥቃት በሶሪያ ጦር ከሚመራው ጥቃት ጋር ተደምሮ እስላማዊ መንግሥትን ከመላ ሀገሪቱ ለማስወጣት ቻለ።
2011 ዓ.ም.
ዕሁድ ሐምሌ 15፣ 2018 የተነሳ ፎቶ ነው፡፡ ደማስቆ አቅራቢያ ምሥራቃዊ ጉታ ክፍለ ግዛት ዱማ ከተማ ውስጥ በአንድ የጦር ሠራዊት የፍተሻ ጣቢያ ላይ የፕሬዝደንት ባሻር አል አሳድ ፎቶ ያለበት የሶሪያ ብሔራዊ ባንዲራ ተሰቅሎ ያሳያል፡፡ (ኤፒ)
የሶሪያ ጦር ምሥራቃዊዋን ከተማ ጉታን መልሶ ያዘ። ወዲያውኑም ማዕከላዊ ሶሪያ ውስጥ በሌሎች በአማፂያን ቁጥጥር ሥር የነበሩ ግዛቶችን እና በስተደቡብ በአማፂያኑ ጠንካራ ይዞታ ሥር የነበረችውን ደራዓ ከተማንም ተቆጣጠረ።
2012 ዓ.ም.
U.S. military convoy drives near the town of Qamishli, northern Syria, October 26, 2019. እ አ አ ጥቅምት 26/2019 የተነሳው ፎቶ የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች በቃሚሽሊ ሰሜናዊ የሶሪያ አቅራቢያ ይታያል፡፡ (ኤፒ)
እስላማዊ መንግሥት በሶሪያ የነበረውን የመጨረሻ ይዞታ አጣ። ሆኖም ዩናይትድ ስቴትስ በኩርዶች አጋሮቿ ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለመከላከል ጥቂት ወታደሮቿን በሶሪያ ለማቆየት ወሰነች።
2013 ዓ.ም.
በስተግራ በኩል የሚታዩት የሶሪያ ፕሬዝደንት ባሻር አል አሳድ እ.አ.አ ጥር 7፣ 2020 ዓ/ም ደማስቆ ውስጥ ከሩስያ ፕሬዝደንት ቭላዲሚር ፑቲን ጋራ በተገናኙበት ወቅት። (ኤፒ)
ሩሲያ የሶሪያ መንግሥት ለሚያካሂደው ጥቃት ድጋፍ ብትሰጥም አብዛኛውን የጦር ግንባር ከምትቆጣጠረው ቱርክ ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት በማድረግ ተጠናቀቀ። በዚህ ወቅት አሳድ አብዛኛውን ግዛት እና ዋና ዋና ከተሞች በመቆጣጠራቸው አገዛዙ ሥር የሰደደ መሰለ። አማፂያኑ ሰሜን ምዕራብ አካባቢዎችን ብቻ ሲይዙ፣ በቱርክ የሚደገፈው ኃይል የድንበር አካባቢን፣ በኩርድ የሚመሩት ኃይሎች ደግሞ ሰሜን ምሥራቁን አካባቢ ተቆጣጠሩ።
2016
ቅዳሜ ህዳር 4፣ 2023 ዓ/ም ደቡባዊ ሌባኖስ ውስጥ ከእስራኤል ጋራ በሚዋሰነውና ‘አይታ አል ሻብ’ ከበተባለ ሥፍራ ወጣ ብሎ በሚገኝና ቦታ በእስራኤል የተፈጸመውን የአየር ጥቃት ተከትሎ ጥቁር ጢስ ሲወጣ ያመለክታል። (ኤፒ)
እ.አ.አ ጥቅምት ሰባት ሐማስ በእስራኤል ላይ ያደረሰው ጥቃት በእስራኤል እና በሂዝቦላ መካከል ሊባኖስ ውስጥ ጦርነት ቀሰቀሰ። በዚህ ምክንያት ቡድኑ በሶሪያ የነበረው ይዞታ በመመናመኑ በአሳድ ላይ ከፍተኛ መዳከም አስከተለ።
2017 ዓ.ም.
እ.አ.አ ታኅሣሥ 6፣ 2024 ዓ/ም የሶሪያን ሃማ ክፍለ ግዛት የመንግሥት ተቃዋሚዎች መቆጣጠራቸውን ተከትሎ፣ በጥይት የተበሳሳ የፕሬዚደንት ባሻር አል አሳድ ፎቶግራፍ ከተሰቀለበት የክፍለ ግዛቱ አስተዳደር ቢሮ ፊት ለፊት እንድ ተዋጊ የሮኬት መወንጨፊያ ይዞ ይታያል። (ኤፒ)
ይህን ጊዜ አማፂያኑ በአሌፖ ላይ አዲስ ጥቃት ከፈቱ። የአሳድ አጋሮች ትኩረት በሌሎች ጉዳዮች በተጠመደበት ወቅት የአሳድ ጦር በፍጥነት ተንኮታኮተ። አሌፖ በተያዘች በስምንተኛው ቀን አማፂያኑ አብዛኞቹን ዋና ከተሞች በመቆጣጠር ደማስቆ በመግባታቸው አሳድ ከሥልጣን ተወገዱ።